ይህ አፕ ከ30 በላይ ምርጥ የሆኑትን የነብያችን ﷺ ባልደረቦች ታሪክ በአጭሩ አካቶ ይዟል። 30+ Verhaal van Sohabs.

Laatste Versie

Versie
Update
30 jun. 2023
Ontwikkelaar
Google Play ID
Installaties
100.000+

App APKs

30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ APP

ስም በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው
የአላህ ሰላትና ሰላም ከፍጡራን ሁሉ ምርጥ በሆኑት በነብያችን (ﷺ) ላይ ይውረድ።

ይህ አፕ ምርጥ የሆኑትን የነብያችን ﷺ ባልደረቦች ታሪክ በአጭሩ አካቶ ይዟል።
ቁርአንን የህይወታቸው ብርሀን አድርገው ይዘውታል። መርሆችና አስተምህሮቶች ወደ ህይወት ለውጠዋል። ምግባር ምጥቀት ስፋትና በአላማ ፅናት እንዲሁም በመልካም ስብዕና ከፍተኛ ደረጃ ለመድረስ በቅተዋል ።
ነብዩም(ﷺ) እንዲህ ሲሉ አወድሰዋቸዋል
"ከሁሉም ምርጡ ትውልድ እኔ የምገኝበት ትውልድ ነው ፣ ከዚያም የሚቀጥለው ፣ ከዚያም የሚቀጥለው ፣ ከዚያም የሚቀጥለው …"
ታላቁ ሶሀባ ዐብደላህ ዒብነ መስዑድ የሶሀቦችን ገድል በዘከሩበት ንግግራቸው እንዲህ ይሉናል፦
"አረአያ ሊሆን የሚችል ስብዕና የሚሻ ካለ የመልዕክተኛው ባልደረቦች ብቻ ናቸው አርአያ ሊሆኑ የሚችሉት እናም የሶሀባ ትውልድ አባላት። ምክንያቲም እነሱ ከማንም በላቀ ሁኔታ የጠለቀ ዕውቀት ባለሀብቶች ነበሩና። ቀጥተኛውን ጎዳና መርተዋል። አላህ ለመልእክተኛው ባልደረባነት አጭቷቸዋል ። የዚህን ዲን ታላቅ አደራ ተሸክመዋል። ማንነታቸውን እወቁ ፣ፈለጋቸውንም ተከተሉ ፣ የህይወት መንገድ የተከተሉ ሰወች ነበሩና።
ቦታና ጊዜ የምንገኝ ሙስሊሞች የዚያ ድንቅ ትውልድ ፤የዚያ ቁርአናዊ ማህበረሰብ አባላት አርአያነት እንደሚያስፈልገን ግልፅ ነው።ከሶሀባ ትውልድ ታሪክ በጣም ብዙ እንማራለን።ከምርጥ ስብእናቸው የጠራ ምንጭ እንጎነጫለን ። ውስጥ ያደረጉት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ለህይወት ጉዟችን ብርሀን ነው ። የማንነታችን መለያ ነው…"።ከቀደምቶች ታሪክ እራሳችንን እንድናስተምር ይህ የሶሀበች ታሪክ የሚለው አፕ አስተማሪ ይሆናል ብለን እናስባለን።
አፕ ታሪካቸው ያልተጠቀሱ ብዙ ሶሀቦች አሉ፤ በአላህ ፍቃድ በየግዜው የሌሎችም ሶሀቦች ታሪኮችን አካተን አፑን በየግዜው እናድሰዋለን፣ ከእርሶ የሚጠበቀው ይህን አፕ በየግዜው ማዘመን/Update ማድረግ ነው።

ተቋዳሽ ይሆኑ ዘንድ አንብበው ለሌሎችም ያጋሩ።

ስራችን የተከበረው የአላህን ፊት ተፈልጎበት የተሰራ እንዲሆን እንዲሁም ታሪኩን ከተለያዩ ምንጮች ላሰባሰቡ ፀሐፊዋች ለኛም በዚህ ስራ ለተባበሩንም በሞት ለተለዩንም ይህንን ስራ ለሚያሰራጩትም ከሁላችንም ዘንድ አላህን እማፀነዋለሁ።

ፍቃድ ሌሎች ጠቃሚ አፖችን አዘጋጅተን በቀጣይ እናደርሳችኃለን።
________________
የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል - ከናንተ ውስጥ መጥፎን ነገር ያየ በእጁ ይቀይር ካልቻለ በምላሱ ካልቻለ ደግሞ በልቡ ይጥላ ይህ ግን (በልብ ብቻ መጥላት) ደካማ ኢማን ነው" (ሙስሊም ዘግበውታል)
እህቶቼ ታሪኩን በምታነቡበት ግዜ ከቁርአን ከሀዲስ የተጨመረ ወይም የተቀነሰ ነገር ካገኛችሁ በአድራሻዬ አድርሱኝ።
ላረመኝ ሰው አላህ ይዘንለት።

ሆይ!ጠቃሚ እውቀትን ከተግባር ጋር ወፍቀን መጨረሻችንንም አሳምርልን አሚን! ከነፍስያዬና ከሸይጧን ሲሆን ሐቅን ከገጠምኩኝ ከአላህﷻ ነው።

አዘጋጅ አብዱራሂም ማህሙድ

በፊት ያዘጋጀነውን የነብያት ታሪክ አፕ በሚከተለው ሊንክ መጫን ይችላሉ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=qissa.anbia.hudasoft
Meer informatie

Advertentie